ትዝታ ጋረደው ፣ ትዝታ
ጋረደው ምነው የኔን ፍቅር ነው የኛን ፍቅር ብቻ ይሄን ዘፈን እያንጎራጎርኩ ሱሪዬን እፈታታለው ፤ ፓንቴን ዝቅ አደርጋለው ከዛ
በቃ ተመስጨ ኩሴን መጣል እንደጀመርኩ ፣ ‹‹ትዝታ ጋረደው ከምትል ፣ ግርግዳው ጋረደው እያልክ አትዘፍንም እንዴ›› አትለኝም ልጂቷ
ክው ነው ያልኩት ፡ ምን ማነሽ አልኳት ደንግጨ ፡ ‹‹ማንም ልሁን›› ልጂቷ ከዛኛው ሽንት ቤት ክፍል እያማጠች ወሬዋን ቀጥላለች
፡ ‹‹ብቻ አሁን የጋረደን ግርግዳ እንጂ ትዝታ አይደለም ብዬ ነው አራሙ›› አለችኝ ጭራሽ
እሷም አንደኔ ወጥሯት
ኑሮ ታዲያ በየመሀሉ ‹እህ፣ እህ› ታበዛለች በኔ ጎን ያለው የሴቶች ሽንት ቤት ውስጥ ተቀምጣ ፣ ታስቀምጣለች፡፡ በጣም ስላናደደችኝ
እንዴ የኔ እህት የት ነው ቆይ የምንትዋወቀው ፣ ደሞስ ምን አገባሽ ፣ ጋሽ ሙሀመድ እኮ ይሄን ዘፈን ሲዘፍን እንዳንቺ አይነቱን
ሽንት ቤት ለሽንት ቤት የምትውል ሴት አስቦ አይደለም ፡ የማታ ጀንበርን እያዩ በባህር ዳርቻ ለተዝናኑ፡ በምሽት ጨረቃ ተቃቅፈው
ለደመቁ ፡ ማሪንጌ ለደነሱ ፡ ለጥ ባለ ቄጠማ ሳር ላይ ለቦረቁ ነው ትዝታ ጋረደው የተባለው እናቱ አልኩኝ በዝርዝር ተናግሬ ሊወጣልኝ…
‹‹እና አንተ አሁን
አዋሳ ወይስ ጣና ሀይቅ ዳር ያለህ መስሎህ ነው ፡ ነው ወይስ ነጭ ሳር ሜዳ ላይ ተንጋለህ የምትዝናና መስሎህ ነው›› ሳልመልስላት
ቀጠለች እረ ‹‹ቆይ ጥንብ ሽንት ቤትና መዝናኛ ቦታ እንኳን ለይተህ አታውቅም እንዴ?›› አለችኝ
እሺ ጨረሽ ተናግረሽ
አልኳት…..‹‹ባልጨርስስ ምን ታመጣለህ›› እንዴ ይቺ ሴትዮ ማን ነው የላከብኝ ስል ለብቻዬ አሰብኩኝ ፡ ቤት ጭቅጭቅ ፣ መስሪያ
ቤቴ ጭቅጭቅ ፣ ሰው ሽንት ቤት እንኳን እራሱን አያዳምጥም ፣ ፈታ አይልም ስል ደሞ ለካ ቀስ ያልኩ መስሎኝ ሰምታኝ ነበረ ‹‹
ስማ ሽንት ቤቱንስ ማን ያንተ አረገው ቆይ?›› ንድድ አለኝ ፡ ፈሴ ሁሉ በቃ ቁርጥ ቁርጥ አለ
ሴትዮ እኔ ነግሬሻለው
እኔ ተይኝ ልራበ……..አንቺም አርፈሽ አርተ…….ውጭ በቃ ምን አለፋቹ
ክፉ ባልና ሚስት መሰልን….
‹‹ኡኡቴ የኛ የተረበሸ
ሰው አልቀረብህም ባክህ አሀሀሀሀሀሀ፡ደሞ ምን በልተህ ነው እንዲህ እንደጀነሬተር እምትንደቀደቀው ፡ አሁን ውጭ ሲያዩህ ሰው ትመስላለህ››
ጉድ ፈላ እምታቀኝ ሰው ናት ማለት ነው ፤ ሀሳብ ያዘኝ ደሞስ አጩሆ እሚፈሳ ሰው ሰው አይደለም እንዴ ፤ ሰው ትመስላለህ ያለችኝ
፡ እሷ እኮ ይሄኔ ከውሀ የቀጠነ ፈሳሽ ይሆናል እምትፀዳዳው
ስል ተፅናናው ነገር ግን እንደጀነሬተር ትንደቀደቃለህ ያለችኝ ነቆራ አልወጣልኝም ፡ ልያትና ይለይልኝ አንቄ ነው እምጥላት ብዬ
በደም ፍላት ስወጣ እሷም ወጣች ፡፡
አቤት ከኔ እርሳቸው አፈሩ ፣ ከኔ እርሳቸው አነሱ ፣
የተከበሩ የባላንባራስ ባለቤት ወ/ሮ አበበች አከራዬ ናቸው ፡ በጣም የገረመኝ በማን አፍ ተውሰው ሲሰድብኝና ስዘልፉኝ እንደነበር
ነው ፣ ለካ ብዙ ሰው ማንነት ውስጥ ብዙ አይነት ማንነት አለ ፣ አውቀው ነው ለካ እንደትልቅ ወ/ሮ በግድ በትልቅ ሴት ድምፅ ነጋ
ጠባ ሰላም እሚሉኝ ፣ ድምፃቸው የአንዲት ዘላ ያልጨረሰች ኮረዳ ነበር እኮ የሚመስለው፣ ልክ ስንተያይ ታዲያ ባንዴ እንደ ዱሮው
ቅይር ብለው ‹‹ውይ ውይ ውይ አንተ ነህ
እንዴ ልጄ ፣ እኔን እንዴት ቀለልኩ ልጄ ያ የመናጢ ልጅ አለ ›› ብለው የሆነ ባለጌ ያሉትን ሰው ስም ጠሩልኝ….
እኔ ግን አፈርኩባቸው
እኔም አብሬ ብቀልም ቅሉ ከሳቸው ግን ከአንድ ባላንባራስ ሰፈር ውስጥ አንቱ የተባሉ ሰው ሚስት ድምፅ ቀይሮ ሽንት ቤት እየተቀጣጠሩ
ሲሰዳደቡ መዋል አዲስ ያልታየ ገመናችን ነው መሰለኝ ፣ ሆ ደሞኮ የሰደቡኝ ስድብ ቆማጣ ያሮጣል በስተርጅና አራዳ ናቸው፣ አይጣልባቹ
አንዳንድ ቀን………ባልተመቸ ስፍራ ከአከራይ ጋር ይጣሏል፡፡
No comments:
Post a Comment