Wednesday, November 5, 2014

ቁም ነገር ይብዛልን

ቀረ አንድ ለናቱ……ርዕዮት እሚባል ፕሮግራም ነበረ…..በ ኤፍ ኤም 97.1 ሁሌ ሀሙስ ማታ ከ 3፡00-6፡00 እና እሁድ ጠዋት ከ 4፡00-6፡30 ይቀርብ ነበረ….
መቸም ለጥሩ ነገር ሲሆን የእነ ነበረ አገር ነን…..ይሄም ነበረ ሁኖ ቀረ….

ሲጀመር የፕርግራሙ ባለቤት ገጣሚና ጋዜጠኛ እንዲሁም ሎውየር ቴወድሮስ ፀጋየ …አመለካከቱና ፍልስፍናው ወደር የሌለው ልጅ ነው……..እናም ልጁ የሆነውን ነበረ እንድንሆን ሀሳቡን እና በጎ እይታውን ሲያካፍለን የቆየው….
ሲያቀርባቸው የነበሩትም ሰዎቻችን በጣም የተማርናበቸው እሱ እንደሚለው ትልቅ የህይወት ገፅ የነበራቸውና የሚነበቡ ሰዎች ነበሩ ፣ ……
በተለይ ለነዚህ ለትርኪ ምርኪ ዘፈኖችና የዘፈን ግጥሞች…ሁነኛ ሀያሲ ነበረ….የአድማጭ ጆሮ ይከበር ብሎ የተከራከረልን ስለ ዘፈን እና ሀሳብ ምንነት….የተረከ የነገረልን….ውብ አመለካከት እና በጎነት የሞላው ፕሮግራም ነበረ…..
አዎ እንደ እኔ የግል አመለካከት ….በአሁኑ ሰአት በጣም ጥቂት በጣት የሚቆጠሩ ፕሮግራሞች ናቸው ምናልባት መደመጥ ካለባቸውም …..በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሁሌም እሁድ ማታ ላይ ከ3፡00 ጀምሮ እስከ 6፡00 ብራና የሬዲዮ ፕሮግራም….ይቀርባል …ያው ሁላችንም ማንበብ የምንወድ ሰዎች ስለንባብ ስለሆነ ብሎም ምርጥ ምርጥ ደራሲያንና ሀያሲያን ስለሚቀርቡበት ልናደምጠው ይገባል ባይ ነኝ …
….ሌላ ደሞ በሸገር ኤፍ ኤም የራሷ የመአዛ ብሩ የጨዋታ እንግዳ የተሰኘ ፕሮግራም አለ….ብዙ ውድ ሰዎችን ያደመጥንበትና ሁሌም የምናደምጥበት ፕሮግራም ነው ነው….ካሁን በፊት እነ ፕ/ር መስፍንን ጨምሮ….ብዙ ሰፊ እይታ ያላቸውን ሰዎች አካፍላናለች 
….ሌላው እና ሱስተኛው ሸጋ ፕሮግራም ደግሞ በዛው በሸገር ኤፍ ኤም….102.1 ላይ ሀሙስና አርብ ማታ ከ 3፡00 እስከ አራት ሰአት ድረስ ዋዘኞቹ የተሰኘ ፕሮግራም በአንዷለም ተስፋዬ ይቀርባል…..በዚህም ላይ ከተለያዩ እያሳቁ ከሚያስተምሩ መፅሀፍት ላይ ያነብልናል….ያስተምረናል ያስቀናል ዘና ያደርገናልም……
ግን ጎበዝ ስንት ሺ ታሪክ ባላት ሀገር ላይ እንዲህ እሚወራ ጠፍቶ ቁም ነገር ጠፍቶ አንባቢና አዋቂ መክኖ እንዲህ ዝም ብሎ እሚጮህ አፈኛ ብቻ ሲበዛ አያሳዝንም ትላላችሁ……ፊልሙ ዝም ብሎ ተራ የሰፈር ቀልድና ቁምነገር….ዘፈኑ የሆነ ጩኸትና ማደንቆር ብቻ አላማው…ገለባ የሆነ ግጥም ይዞ በድፍረት የሰው መንፈስ ለመበረዝ ዘልበም ብሎ መልቀቅ…..በዚህ ላይ ከነሱ ድፍረት በተጨማሪ በየኤፍ ኤሙ የነሱን ገለባ ማራገፊያ ሲያረጉን….ምርርርር ብሎን….እንደለመድነው ወደ ዱሮ ቲያትራችን….ወደ ዱሮ ፊልሞቻችን…ወደ ዱሮ ዘፈኖቻችን ተመልሰናል….
ዱሮን እየኖርን ነው….እንደ ዱሮ ሁነን እየተኩራራን ነው….ዱሮን ናፋቂዎች ያረጉንን ጥበብ ሳይገባቸው ጥበብ ላይ የሰፈሩትን እንደ ጢንዚዛ የሚጮሁ ነፍሳቶችን ግን እግዚሀር ለኛ ለምስኪን ባለጆሮዎች እና ባለ አይኖች ሲል ከመድረክ አንጠልጥሎ አውጥቶ እራቅ አርጎ ይወርውርልን.…ድፍረቱን ይንሳልን…ሌላ ምን እላለሁ……
ቢቻልማ ከነሱ በላይ ህዝብ የሚጠብጥና የሚያሸብር አለን?...ጆሯችንን ያለ ይሉኝታ ሲጫወቱበት…አይናችንን በትርኪ ምርኪ….ሲያደበዝዙት ከዚህ በላይ ማሸበር አለን…?
አንዳችም መንፈስ የማያጎለብት…..ስብዕናን የማይጠግን…..ማንነትን የማይነግር ከንቱ ተረት መስበክ….ከዚ በላይ አሸባሪ አለን?.......
ብቻ ግን እኔ እንዲህ አልኩ ይህ የግሌ አመለካከት ነው…..ከላይ እንደጠቀስኳቸው አይነትና እንደ ቴወድርስ ፀጋየ አይነት ፕሮግራምና ሰውም ጭምር ያብዛልን ቁምነገር አዘል ፕሮግራሞችን ያብዛልን…..አበቃሁ..፡፡

No comments:

Post a Comment