Tuesday, April 23, 2013

እንዲህ ቢሆን…..



እንዲህ ቢሆን…..



                                                        በካሌብአለም

በቃ ሁሌም ተመስጌን ማለት ይልመድብን፣ ከኛ በታች ሆነው በኛ የሚቀኑ አሉና፣የኛን ቦታ የሚመኙ ብዙሀን ናቸውና፣ ባለን ነገር እንርካ ይህ ሲባል ደግሞ ተጨማሪ መስራትና መለወጥን አትሞክሩ እያልኩ አይደለም፣የሰው ልጅ ሁሌ ግንባሩን ቋጥሮ ተኮሳትሮ ደስታ እርቆት እንዲኖር ከሚያደርጉት ምክኒያቶች ዋነኛው ነገር እራሱን ከሚበልጡት ጋር ማወዳደሩ ነው፡፡ለምን የበለጡንን ሰዎች ብቻ እናያለን እኛ የበለጥናቸውስ ብዙዎች አይደሉምን? እሚበልጡን ያልናቸውን ሰዎች እራሱ እኛ ደግሞ እነሱን እምንበልጥበት ብዙ መንገድ አለ እኮ፣ ለምሳሌ በብር የሚበልጠንን ሰው እኛ ደግሞ በእውቀት ልንበልጠው እንችል ይሆናል፣ በእውቀት የበለጠንን ሰው እኛ በፍቅር እንልቅ ይሆናል፣ ብቻ ፈጣሪ ለሁሉም እሚበጀውን አንዳች መክሊትና ፀጋ ሰጥቶታል ስለዚህ የምን ማወዳደር ነው በቃ ለራሳችን ባለን ብዙ ነገር መደሰት እና ተጨማሪ ሲያስፈልገን መስራት ብቻ ነው በቃ፡፡ደግሞ ምናለ መሰላችሁ የሆነ ስላለፈ ጉዳይ መጨነቅና ስለነገ እንዴት ብዬ እውላለሁ፣ ምን እበላለሁ ምናምን ብሎ ማሰላሰል ነው ብዙ ጊዜ ደስታ የሚያጣን፣ ቆይ ዛሬ ከዚች ደቂቃ አይደለም ሰከንድ በኋላ ለመኖሩ እርግጠኛ የሆነ ሰው ማን ነው እረ?
ስለ ነገ አትጨነቅ ወይንም አታስብ ሲባል ብዙ ጊዜ ሰዎች እንዴት ህልም አልባ ራእይ አልባ እንሆናለን ይላሉ፣ ነገሩን ዛሬ ደፋፍታችሁ ኑሩ ከሚሉ እሳቤዎች ጋር ያያይዙታል ነገር ግን እንዲያ ለማለት ተፈልጎ አይደለም፣ ሁሉንም እሚያውቅ ፈጣሪ ነውና አጉል ነገን በቅጥጥርህ/ሽ አስመስለህ/ሽ የዛሬን ደስታ አታባር/ሪ ለማለት ነው፡፡ ከምንም በላይ ለኔና ለናንተ እርግጠኛዋ ሰአት ይህች ያሁኗ እምናወራበት ሰአት ናት፡፡
ያደጉቱና የተመራመሩቱ ወዲያ ማዶ ደስተኛ ሆነው የሚኖሩቱም ዜጎች scientific life ብለው የሚጠሩት ይህንኑ አይነት ጭንቀት የሌለበት ዘና ብሎ በፍቅርና በደስታ የሚኖርበትን ቀላል ህይወት ነው፡፡ በቃ ነገሮችን ማቅለል፣ ጥሩ ጥሩውን ማሰብ፣ ሁሉንም የሰው ልጅ እኩል ማየት መውደድ በቃ ያኔ እርግጠኛ ነኝ ፍቅር ይሞላል ፍቅር ካለ ደግሞ ሁሉም አለ ሁሉም ደግሞ የሚሆነው ሁሉንም ለበጎ ነው ብለን መቀበል ስንችል ነው፡፡ ለበጎ ነው ማለት ይልመድብን ይህች እንግዲህ የዚህ ሳምንት ምክሬ ናት ቻው፣ባይ ባይ…..

No comments:

Post a Comment