Thursday, April 4, 2013

Different views of Articles



ጥበብ ያለዉ ህይወት ፍቅር  አለው
                               

                                                  በካሌብ አለማየሁ

                                               
ስነ-ፁሑፍ የዘመንና የህይወት ሀውልት እንደሆነ በስነ-ፁሑፍ ሙያ ውስጥ ያለፉ አያሌ ሊቃውንቶች ይገልፃሉ፡፡ ስነ-ፁሑፍ ሲባልም በውስጡ ግጥም አጭርና ረጅም ልብወለድ እንዲሁም ተውኔቶችን በአጠቃላይ የጥበብ አምድን ይዳስሣል፡፡ ህይወት ደግሞ በቃ የምንኖረው የማህራዊ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ህይወት ውጤት ነው፡፡ እነዚህን የጠቀስኳቸውን ሒደቶችና ኩነቶች ደግሞ ጥበብ በጠበብተኛዋ በቃል ሀረግ መረዋዋ አቀናጅታ የህይወትን ክንፍ አክናፍ ጨብጣ የበቀለበትን እትብት ጎረጉራ ተሣያለች፡፡ ሠቆቃ የሆነው ህይወቃችነ በጥበብ ሲገለፅ የበለጠ ሠቆቃውን አሠማምራ ሀቁን አጉልታ ታሣየናለች፡፡ ሐሴት የሞላበትም ከሆነ በግጥም በዝማሬ በቃላት ድርድራ ጥርስ ያወጡ የፈገጉ እውነቶችን እንዳለ ደስታ እንደተናነቃቸው እያነበብን እንድንደሠትባቸው እየኖርንም እንድናደምጣቸው አድርጋ ትገልፃለች፡፡

ፈጣሪ አለምን አብለጭላጭ አጓጊ አድርጎ ሲስላት ሠዎቸ እና በላይዋ ላይ የሚኖሩ ፍጥረቶችም ተብለጨለጩባት ከፈጣሪም ዘንድ ሊወጡ ደረሡባት እናም እንቅፋት ሆነችባቸው፡፡ እንቅፋት ሲበዛ ያደማል፡ዉስጥ ይሰብራል ስብራት ደግሞ እንዳች መጥፎ ሽንፈትንና ሀዘንን ይፈጥራል፡፡ ሀዘን ሰህይወት ያውም ቆጥረን ይህን ያህል እንኑር ብለን ላልተረከብነው የህይወት እድሜ ዘመን ይመራል፡፡ እናም መራራ ህይወትን ለማጣፈጥ እንደ ወይን እየጣፈጠ እሚወርድ፡ እንደ ከርቤ መአዛው እየተሣበ ወደ ውስጥ እሚሠርግ እነደ ጀምናስቲክም ሠውነትን እሚያፍታታ ጥበብ ያስፈልጋል፡፡ በጥበብ መመሰጥ ውስጥ በቃ ስራ ፈት ነፍስ አትኖርም ፡፡ አንዳች ብሒል ያዘለች ለኑሮ መምረር እምትጨነቅ በጎ ፈቃድን ሁሉ የምትሻ ፅናትና ብርታትን፡ ማድመጥና ማገናዘብን ሁሌ ከእቅፏ የማትለይ እንቁ የፈጣሪ ስጦታ ናት እሷ፡፡ እናም ሎሪቱ መቸም ድንቅ ሀሣቢ ሀያል የጥበብ ሠው ነበርና እኔም የሱን ግጥም ስለጥበብ ስለፍቅር ስል እንደምሳሌ ልጠቀማት ነው፡፡ ደግሞም ሠርቶልን ያለፈው የሡን ብርሀን ለሌላ እንደናፀባርቅ የሡን መሻት ለሌላ እንድናሰተላልፍ ትውልዱም የነፍስ ብርሀን የፈጣሪ ቃል እንዲገባው የህይወት ትግል እንዲያፀናው ግድ ይላል፡፡

ፈራን ፍቅር ፈራን
ልጅነት የለገሠንን
የፍቅር አምላክ በጥበብ
በረቂቅ ያለበሠንን
በመለኮት የቀባንን
ህብረት ፈራን
ፍቅር ፈራን…. ይላል ፀግሽ እዚህ ላይ ተመልከቱ ፍቅር፣ልጅነት፣ ጥበብ፣ መለኮት፣ ህብረት፣ በመጨረሻም ጠቅላያቸው አምላክ አለ፡፡ ስለፍቅር ሲባል ሞኘ መሆን እንዴት ደስ ይላል ልክ እንዲያ እንደ ህፃኑ እንደ ቦቀቅላው ምንም ሣያወቅ ሁሉን እንደሚጠጋው፣ አዎ አሱን ነው ልጅነት ያለው፡፡ ልጅ ሆነን ስንጣላ እርቃችንም ወዲያው ነው፣ ሆደ ቡቡ ቦርቧራ ገራገር የዋህ እምንላቸው ቃላቶች በሙሉ የእውነት እግር አውጥተው የኖሩት ያነ በልጅነት ነው ልጅነት ምንም አያውቅም በቃ መቦረቅ ነው ፣ ደስታ ነው እንደ ወንዝ እሚፈስ ከዚያ ወደዚህ እሚለጋ ፍቅር ነው፡፡
እናም ፍቅር በልጅነት በጥበብ በመለኮት ረቂቅ ሆኖ ይኖራል፡፡ የነዚህ ሁሉ ባለቤት አምላክ ነው፡፡ እናም ለዛ ነው መሠለኝ ሎሬቱ አቀናጅቶ በለዛ አዋዝቶ ልጅነት የለገሠንን፣ የፍቅር አምላክ በጥበቡ በረቂቅ ያለበሠንን እያለ የቀመረው፡፡ ነገር ግን ይህን ሁሉ ብሎ ሲያበቃ ሁሉንም ፈራን ነው እኮ ያለው፡፡ እሱ የኖረበት ዘመን ህብረት ከነሣው የኔውማ ይኸ ትውልድ ነፍሡን አካቶ ባይነሳው ነው እሚገርመኝ፡፡ እኔ በሃያዎቹ አጋማሽ እምገኝ ወጣት ነኝ እናም አያቴ ቅድመ አያቴ እንዲሁም የሠፈርና የሀገር ሽማግሌዎች ሲነግሩኝ ዱሮ ቁርጥ ርካሽ እንደሆነ ወይን በየሠፈሩ እንደሚገኝ የማር ጠጅ ለተራ የኔብጤም እንደሚሠጥ ፤ በሦስትና በአምስት ብር የዛሬውን 2000 ብር ሙክት እንደሚገዙ ብቻ በአጠቃላይ ኑሮው ርካሽ እንደነበር ነግረውኛል፤ ሠውም ትንሽ ስለነበር ተጠራርቶ ሠርጉንም ሀዘኑንም አብሮ በልቶ አብሮ ጠጥቶ ነው እሚያሣልፈው ሁሉም ይነፋፈቃል ይተዛዘናል ለወገኑ ለደንበሩና ለሀገሩ ፣ ለማንነቱም እማይቆረቆር እልነበረም፡፡  ይሁን እንጂ ሆድ እየተራበ ነፃነት እየተሠለበ ጥበብ አይጣፍጥም፡፡ ነገር ግን የዋህነት ፡ቅንነት፡ ፍቅር ካለ፣ መዋደድ ካለ ሣንበላ እንጠግባለን፡ በመተሣሠብ ክፍተታችን ይሞላል፡፡ ግን እንትን ነስቶናል ምን ነበር ያለው ፀግሽ ህብረት አዎ ህብረት ማለት እንደነት ነዉ፡፡ እኛ ሣይታወቀን በፍቅር በመዋደድ የእግር ብረት ጠንጎ ቆፍድዶ የሚያሰተሣሠር አንዳች ከፈጣሪ የተሠጠ በልጅነት ወቅት የተለገሰነው እንደገና አብቦ የሚያያይዝ ፍቅር፡ ሀብረቱንም ፍቅሩንም የነሣን ግን ኑሮውና ፓለቲካው ነው፡፡ ሆድ ጭብጥ አፍ ልጉም ሲል ጥበብ እምታፍታታው ቁምአካል  እምትተነፍሠው ነፍስ ብቻዋን አቅም ያንሣታል፡ ይህም አይነቱ ህይወት ልክ እንደ ዛፍ ነው ፡፡ ምክንያቱም ዛፉ በነፋስ ሀይል ይወዛወዛል ነገር ግን ካልጠጣ ውሀ ካለገኘ በደረቅ ወቅት ይደርቃል፡ በዝናብና በክረምት ደግሞ ይለመልማል፡፡ ነገር ግን ልብ በሉ እስካሁን ሲደርቅም ሲረጥብም በነፋስ ሀይል ይወዛወዛል እኩል ዛፍ ነኝ ይላል፡፡ የእኛም ኑሮ እንግዲህ እንዲህ ነው፡፡ የፍቅር አምላክ በጥበቡ በረቂቅ ያለበሠን በመለኮት የቀባን ህያው ፍቅር ባይኖር ፣ ቸርነት ባይኖር በዚህ ጡዘት ዘመን በጠፋን ነበር፡፡ ነገር ግን ከውጪ አለም ስንወዳደር እንደ ደረቁ ዛፍ በአምላክ ሀይል እየተወዛወዝን በግድ ሠው ነን እምንል አልሞት ባይ ተጋዳዮች ነን ምክንያቱም አልኖርንማ፡ አንድንኖርም አልተፈቀደልንማ፡ ህብረት ጠፍቱል፡ ፍቅር ትፍቱል፡፡አምላክ የሠጠንን ነገር አንፍራ፡ አምላክ በቸርነቱ የተዋሀደንን አንጥላ፡፡ እናም በቃ እምንለውን በቃ እያልን ሀሤት ተድላና ምቾትን የምታፈልቅ ህያው ጥበብን ግን እናድምጥ ማድመጥ ማለት መመሰጥ ይሁን ከልብ እንደሠት፡፡ 

"A reading society is a leading society" T.J

 By Kaleb   Alemayehu

There is a great saying by Mark Twain that a man who does not read good books is no different from the man who cannot read them. He is absolutely correct in saying so. Books can be said to be the best bargains around the world.

This does not mean that while start reading any book, a book may cost only $20 but the time spent in reading it is priceless. If your time is worth $200 per hour then one should read a book which is worth at least thousand dollars.
Choosing the right book can make a lot of difference. Choose a book which is in alignment with your personal and professional goals. After reading such book your mind will be filled with great thoughts and knowledge which will lead you towards greater achievement in life.
While reading a book highlight or underline the key points. Make sure you look for points related to your specific needs and interest and mark them. This will let you filter through different messages provided in the book; and then you can narrow down your focus to the specific ideas useful to you. The book should be based on three main aspects autonomy as it has the ability to influence our world; mastery which allows us to grow, evolve and learn; purpose gives us a meaningful work and contribute to our world. A book which we select should fulfill these three criteria.
Book is only useful when you review it and install its ideas in your life. Once you have finished reading the book, put aside it and review it for a week. After that go back to the sentences or pages which you have underline in order to follow up the top ideas. Do this exercise for a week; make a list of follow up items on which you need to execute. You need to understand that there is no point capturing all these valuable ideas if you do not wish to follow them up. They are completely worthless without a follow up plan. So make sure you have one as soon as you finish capturing the ideas, you should be ready for some action.
After that, put these new actionable items into your calendar. Do not be furious in completing these actions; make sure you give yourself enough time to complete these things. Also make sure you leave yourself enough time for priorities in your life.
Books have a great impact on our life, what we read is bound to have some effect on us. Now you need to decide what would be that affect, it could be good as well as bad. Now you need to decide how, when and what impact are books going to make in your life. Start reading a book from today onwards and you will realize the difference very soon. Apart from all these also take a look at the 10 benefits of reading as the following:
1. Reading is an active mental process: Unlike sitting in front of the idiot box (TV), reading makes you use your brain, while reading you would be forced to reason out many things which are unfamiliar to you. In this process you would use the grey cells of your brain to think and become smarter.
2. Reading improves your vocabulary: Remember in elementary school when you learned how to infer the meaning of one word by reading the context of the other words in the sentence? You get the same benefit from book reading. While reading books, especially challenging ones, you will find yourself exposed to many new words you wouldn’t be otherwise.
3. Gives you a glimpse into other cultures and places of the world: How would you know about the life of people in Kenya if you don’t read about it? Reading gives you an insight into the diversity of ethnicity of people, their customs, their lifestyles etc. You become more aware about the different places and the code of conduct in those places.
4. Improves concentration and focus: It requires you to focus on what you are reading for long periods. Unlike magazines, Internet posts or e-Mails that might contain small chunks of information, books tell the whole story. Since you must concentrate in order to read, like a muscle, you will get better at concentration.
5. Builds self-esteem: The more you read, the more knowledgeable you become. With more knowledge comes more confidence. More confidence builds self-esteem. So it’s a chain reaction. Since you are so well read, people look to you for answers. Your feelings about yourself can only get better.
6. Improves memory: Many studies show if you don’t use your memory, you lose it. Crossword puzzles are an example of a word game that staves off Alzheimer’s. Reading, although not a game, helps you stretch your memory muscles in a similar way. Reading requires remembering details, facts and figures and in literature, plot lines, themes and characters.
7. Improves your discipline:
Making time to read is something we all know we should do, but who schedules book reading time every day? Very few, that’s why adding book reading to your daily schedule and sticking to it, improves discipline.
8. Improves creativity: Reading about diversity of life and exposing yourself to new ideas and more information helps to develop the creative side of the brain as it imbibes innovation into your thinking process.
9. You always have something to talk about: Have you ever found yourself in an embarrassing situation where you didn’t have anything to talk about? Did you hate yourself for making a fool of yourself? Do you want a remedy for this? It’s simple. Start reading, Reading widens your horizon of information. You’ll always have something to talk about. You can discuss various plots in the novels you read, you can discuss the stuff you are learning in the business books you are reading as well. The possibilities of sharing become endless.
10. Reduces boredom: One of the rules I have is if I am feeling bored, I will pick up a book and start reading. What I’ve found by sticking to this is that I become interested in the book’s subject and stop being bored. I mean, if you’re bored anyway, you might as well be reading a good book, right? If you want to break the monotony of a lazy, uncreative and boring life, go and grab an interesting book. Turn the pages to explore a new world filled with information and ingenuity.




ህይወት ሀሳብና ነጻነት

                                                        በካሌብ አለማየሁ

የሰዉ ልጅ ሲፈጠር ከስጋና ከነፍስ ጥምረት ነዉ፡፡ ስጋዉ ተገንብቶ ሲያበቃ ፣ እፍ አለበት ፣ ይላል፡ ቅዱስ መጽሀፉ፡፡ ያቺ እፍ የተባለች ነገር ፣ ነፍስ ሆነች ፣ ነፍስን ካገኘ በኋላ ፣ የሰዉ ልጅ ማሰቢያ አእምሮ ስራዉን ጀመረ ፣ ልቡናና ሌሎች የተገጠሙለት ነገሮች ሁሉ በስርአት ስራቸዉን ጀመሩ፡፡ እኚህን ሁሉ ነገሮች የሰጠ አምላክ ፣ የሰዉ ልጅ ልቦናዉ የፈቀደዉንና አእምሮዉ የሚያስበዉን ነገር በትክክል ይፈጽም ዘንድ ፣ ባሻዉ መንገድ ይተገብር ዘንድ ፣ ፈጣሪ ነጻነቱንም ሰጠዉ፡፡ እናም “ህይወት ፣ ሀሳብና ፣ ነጻነት አንድም ሶስትም ናቸዉ፡፡” ያለዉ ካህሊል ጂብራን እዉነቱን ነዉ፡፡ “ሀሳብ ያለ ነጻነት ግራ እንደተጋባ መንፈስ ነዉ ፣ ህይወት ያለ ሀሳብ ነፍስ እንደሌለዉ አካል ነዉ ፣ ነጻነት ያለ ህይወት እንደ ግኡዝ አካል ነዉ፡፡” ይላል ካህሊል ጂብራን፡፡
የሰዉ ልጅ ከእንስሳ የሚለየዉ በማሰቡና በማገናዘቡ እንደሆነ መቸም ሶስተኛ ክፍል ተማሪ የሚያዉቀዉ ሀቅ ነዉ፡፡ነገር ግን እንዲህ በቀላሉ እየተናገርን ያደግነዉ ቃል “ሀሳብ” እጅግ በጣም ከምገልጸዉና ከምንለዉ በላይ ከባድ ነገር ነዉ፡፡ሀሳብ ሰዉን ከእንስሳ ብቻ አይደለም ፣ ሰዉን ከሰዉ ፣ ሰዉን ከራሱ ከፈጣሪ ሁሉ የለየ ታላቅ መሳሪያ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ሰዉን ከሰዉ ስንል ፣ በእስር ቤት ያለዉን ካልታሰረዉ ፣ የተማረዉን ካልተማረዉ ፣ በአደጉ አገሮች የሚኖሩትን ባላደጉት አገሮች ከሚኖሩት ፣ በከተማ ያሉትን በገጠር ከሚኖሩት ፣ገዢን ከተገዢ ወይንም ህዝብን ከመንግስት እና ከሌሎችም እጅግ ብዙ ያልተገለጹ የየእለት ኑሮአችን ላይ ሁሉ አስተሳሰባችን እራሱን ሰዉን ከሰዉ ይለያል፡፡ ይህን ታላቅ ነገርን “ማሰብን” የሰጠዉ ደግሞ ታላቁ ህያዉ ፈጣሪያችን ነዉ፡፡ እሱ የሰጠዉን ደግሞ ተፈጣሪዉ የሰዉ ልጅ በየትኛዉም ስልጣኑ ሊሽረዉና ሊቀርፈዉ አይችልም፡፡ ለዛም ነዉ ቶማስ ጃፈርሰን “ህይወትን የሰጠ አምላክ ነጻነትን አብሮ ሰጥቷል” ያለዉ፡፡የሰዉ ልጅ በማሰቡ ብዙ ለመግለጽ የሚታክቱ ታምራቶችን ፈጽሟል፣ እየፈጸመም ነዉ፣ለወደፊቱም ይፈጽማል፡፡ኑክሌር የሰራዉ ፣ አስገራሚ አዉሮፕላኖችን ፣ መንኮራኩሮችን ፣ ያለሰዉ የሚነዱ አዉሮፕላኖችን ፣ ጀቶችን ፣ አስገራሚ የሞባይልና የኮምፒዉተር ቴክኖሎጂዎችንና ካሜራዎችን ፣ ነባዘርን አቆይቶ የእናትን ማህጸን ተክቶ ሰዉ የሚፈጥር መሳሪያዎችን ፣ ጾታ የሚቀይሩ ማሽኖችን ፣ የተለያዩ ስለራሱ ስለ ሰዉ ልጅ የአሁንና የወደፊት ችግር መፍቻ ፣ ሀሳቦች መግነጢሳዊ በሆነ የጥበብ እዉቀቱ ፣ በአጠቃላይ ከሳይንስ እስከ ማህበረሰባዊ እዉቀቶችና ጥበቦች ይህን ሁሉ አስገራሚ ነገሮች የሰዉ ልጅ የከወነዉና የሚከዉነዉ ማሰብ በመቻሉ ነዉ፡፡
ማሰብ መቻል ታላቅ የፈጣሪ ለሰዉ ልጅ የተሰጠ ስጦታ ነዉ፡፡ይህን ሁሉ ነገር ያስብና ይተገብር ዘንድ ፣ ባሻዉ መንገድ ይጠቀምበት ዘንድ ፣ መጥፎ ሀሳብና ተግባር እንኳ ቢሆን የፈለገዉን ያደርግ ዘንድ ፣ ፈጣሪዉ ነጻነትን ሰጥቶታል፡ እርሱ የመጀመሪያዉ ዲሞክራት ነበራ፡፡
ግና እንዳልሆነ ሆኖ ኢትዮጲያ ዉስጥ እንዳሻችን አስበን አናዉቅም ፣ ምናልባትም ያለማደጋችንና ደሀ ተብለን የመጠራታችን ሚስጥርም ይሄ ይሆናል፡፡ ምክኒያቱም በየዘመናቱ የነበሩ የፖለቲካችን መሪዎች እነሱ በፈለጉት እንጂ እኛ በፈለግነዉ ፣ መሆን በፈቀድነዉ መልኩ ስናስብ አልኖርንም ፣ ተለክቶና ተሰፍቶ ነዉ ሲሰጠን የኖረዉ ያለዉም፡፡ ሰዉ ፈጣሪ የሰጠዉን ዕምቅ ጥበቡን አዉጥቶ ይጠቀም ዘንድ ፣ ነጻነትን ይፈልጋል፡፡ይህች ነጻነት ግን አንድም ቀን አምሮባት በኢትዮጲያችን ሳትታይ ቀን ቀንን ተክቶ ይሄዉ ዛሬም አለን፡፡ ያኔ ያች በነጻነት የማሰብ መብት ስምምነት በዉልና በግልጽ ተቀምጣ ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ዕንዲህ ባልፈነጩብን ነበር፡፡
በታሪክ እንደሚታወቀዉ በዉጭ ወራሪ ባለመገዛታችን ኢትዮጲያ ከአፍሪካ በቅኝ ካልተገዙት ሀገራት ዉስጥ ሁል ጊዜ ትጠቀሳለች፡፡ ነገር ግን እኛዉ ከኛ መች ነጻ ወጣን ፣ ለዉጭ ወራሪዎች ሀይል ያሳየነዉ ወኔና ተግባር በራሳችን ሀገር በቀል ፋሺስቶች ግን ጸጉረ ልዉጥ ስላልሆኑ ነዉ መሰል ፣ ወኔያችን ሞቷል ፣ ስሜታችን ቀዝቅዟል ፣ ብዙ የመጻፍ መብታችን ፣ የሰላማዊ ሰልፍ መብታችን ፣ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታችን ፣ ይህ ሁሉ መብቶቻችን ተጥሰዉና ተጨፍልቀዉ ሳለ አንዳች ድብታ ፣ የሆነ አዚም ነገር የጣለብንን እንጃ ዝም ያለ ምስኪን አዲስ ትዉልድ መጥቷል፡፡ ዝምታዉ በጣም ያስፈራል ፣ ምክኒያቱም የማይቻለዉን ነዉ የቻልነዉ ፣ ማንም በዚህ በተለይ በዲሞክራት አለም ፣ ያልሰራዉን ነጭ ለባሽ ሲባል ፣ ከመሬት ተነስተዉ አሸባሪ ሲሉት ዝም የሚል የለም ለዛም ነዉ ቪክተር ሁጎ የተባለ ጸኀፊ “One can resist the invasion of an army but can’t resist the invasion of ideas.” ያለዉ፡፡
ለማንኛዉም ማናችሁም ፍጡራን ባለስልጣኖች ሆይ “ተንበርክከን ከምንኖር ቁመን ብንሞት ይሻለናልና” አስቡበት እኛም እናስብበታለን፡፡




ታሪካዊ ተዉኔቱና አሁንነት

                                                                 በካሌብ አለማየሁ


መቸም ኪነ ጥበብ መዝናኛ ብቻ ሳይሆን መማሪያ ፣ መልእክት ማስተላለፍያ ፣ ገሀዱን አለም ማሳያ መስታወት ነው፡፡ ነፍሱን ይማረውና በአንድ ወቅት ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ቴዎድሮስ በሚል የሰራው ተውኔት ልቤን ቢነካው የቃላቶቹ ታሪክን ቁልጭ አድርጎ አጥርተዉ በሩቁ እስከ አሁን ድረስ ተሻግረው ዛሬ ላይም ታሪኮቹ እውን ቢሆኑብኝ ነው ይህችን ፅሁፍ ልፅፍ የተሰናዳሁት፡፡
ካሳ የኢትዬጵያ አንድነት ሲመኝ ሲጓጓ ሲተልም እንደሞተ እናውቃለን ፡፡ ነገር ግን በዙሪያው የነበሩ ነጋሲያን አስቸግረውት ኋላም እንግሊዝ መጥቶ ተዋግቶት እራሱን በራሱ ድል እንደነሳ እናውቃለን፡ የሎሬቱ ተውኔት እውነተኛውን ታሪክ ተደግፎ ነው በሚገርም የፈጠራ ክህሎቱ አሳምሮ የተረከውና የከየነው ፡፡ እናም በዚያ ተውኔት ውስጥ ያሉት የካሳ ንግግሮች ዛሬ ላይም ለአሁኗ ኢትዬጵያ ገሀድ የሆኑ አሉ ፡፡ የመድረኩ ካሳ አንደበት እንዲህ ሲል ነበር፡-
እኔን እጅግ ያሳሰበኝ የህዝብ አንድነት ሚስጥሩ፣
የሀገር አንድነት ደም ስሩ፣
የኢትዬጵያ ህልውና ክሩ፣
ይላል በሸዋ በትግሬ በላስታ ያሉት ነጋሲዎች የእሱን አንድነት አልሰማ ቢሉት ፣ዝቅ ይልና ሌላ ያነበንባል …
…..ከቶም ነብሴን የሚጨንቀው
እስከመቼ ድረስ ይሆን ይህ ኢትዬጵያዊነት ስሙ
ለነጋሲና ለህዝቡ ልዩ የሚሆን ትርጉሙ
እስከመቼ
ኢትዬጵያ ስንል ውስጣችን ሁለት ገፅ የሚሳለው
ቀማኛ መልኳን በስልጣን ደሀ ግን በእናት እሚያይው
ሲል ዛሬ ላይ እውነት የአሁኗ ኢትዬጵያ ነጋሲዎችስ የነሱና የኛ ኢትዬጵያ አንድ ናትን ስልጣን ሲይዙና ሳይዙ ፣ ወንበሩንና መንበሩን ከጨበጡና ሳይጨብጡ ያላቸው ኢትዬጵያ አልተለየምን
እሚል ጥያቄ ለራሴ ጠየኩኝ፡፡ አዎ ይህ መንግስት ደርግን ለመጣል ሲታገል ብዙሀን ትግሬ ተወላጅ ቢኖረውም ነገር ግን የሌሎችም የኢትዬጵያ ህዝቦች በጎ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ይሁን እንጂ ነፃነትክን እሰጥሀለው ፣ ስልጣን ለህዝብ ይሆናል ፣ ሁሉም ብሄር ፖለቲካዊ መንበሩን ይዳኛል ይሳተፋል ብሎ ሲያበቃ የፈለጉትን የዙፋን በትር ካገኙ በኋላ ግን የነሱዊቱ ኢትዮጵያ ሌላ የኛይቱ ሌላ፣ ካሳ በዚያ ተውኔት ላይ ንግግሮቹ ይከብዳሉ፣ ያሳዝናሉ ፣እሩቅ መጥተው ዛሬም ይሰማሉ ክብር ለሎሬት ፀጋዬ ይሁንና፡፡ መንባንቡ አላለቀም፡-
……. የመጠላላት ቂም ውርሱን ከአጥንቱ ውስጥ ለመንቀል፣
የሀቅን ቅርስ ለትውልድ ለማስቀረት ሰው ለማብቀል፣
የኢትዮጵያዊነትን ሀሁ የኢትዮጵያዊነትን ፊደል፣
ለማስቆጠር እንዴት ልበል
ዛሬስ የኛን እስቲ እንየው እውነት ሀቅ ፍቅር አለን ገና እንዲህ አስበሀል ተቃውመሀል እንዲህ እንብበሀል እንዲህ ፅፈሀል ተብሎ አይደለ እንዴ እስር ቤት የሚሰደደው የእከሌ ዘር ተብሎ አይደለ እንዴ ዙፋን የሚሰጠው ሀሳቡ ታይቶ ማንነቱ የሚጠላበት ሀገር እኮ ነው የተፈጠረው፣ ስልጣን ሲጨብጡ አጥንት እንደያዘ ውሻ አንደኛው ባለስልጣን ሌላኛው ላይ ያጉረመርማል፣ አንዱ ብሔር ሌላኛውን በአይነቁራኝ ያያል መጠላላትና ቂም በአጥንታቸው ውስጥ ፀርሷል፣ ጭራሹኑ ለማን እንደሚያገለግሉ ለየትኛው ህዝብ እንደተወከሉ ዘንግተው ኢትዮጵያን ተረት አርገዋት እየተረቷት አንኩ እንቆቆልሽ እያሉን የማይፈቱት፣ የሰረዙት ከአይነ ሕሊናቸው የገደፉትን እውነት ነው እንግዲህ ለማስቆጠር እንዴት ልበል ያለው ፀግሽ
………. የህዝቡን የማንነት ክብር እንደ አውሬ ቁልቁል በመስበር፣
ይኽው በጎሰኝነት ዕድፍ ብቻ ታውሮ ታሞቆ፣
ተድናቁሮና ተናንቆ፣
የሰብዓዊ ህልውናው ከልቦናው ስር ተነጥቆ፣
ይላል የካሳ ገፀ ባህርይ በታሪኩ እንደተጠቀሰው የኮሶ ሻጭ ልጅ አይነግስም ብለው ስለናቁት፡፡
የመድረኩ ካሳም እንዲህ እያለ በምሬት ያነበንባል፡-
….ቀድሞም ቢሆን ከውስጥ ነው፣ የነጋሲ ፍልና ሽል፣
ቅጠሉን መስሎ ስውር ትል፣
ዛፉን ቦርቡሮ እንደሚጥል፣
ካለ በኋላ ውስጡ ያልወጣለት ባለታሪኩ፡-
….በዘውድ እየተናነቀ አንድነትሽን ሊያራክስ፣
በጎሳ እየከፋፈለ ደሀ ወገኔን ሊያጫርስ፣
እኔን በመግደል ክብርሽን ቅድመ ታሪክሽን ሊያንኳስስ፣
ይላል በዘመኑ የነበሩት ንጉሳዊ ዝርያዎች ሲያስቸግሩት፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ በመኖር በመብላት እንግዳ በመቀበል በፈሪህ እግዜአብሔር የሚኖር ህዝብ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ የተውኔቱ ካሳ የተረከበው ታሪክ አሁን ላለው ትውልድ ጉድፍ ሀቅ ነው፡፡ ነፍጠኛ ምናምንቴ እያሉ እርስ በራሱ እንዲጠቋቆም ነጭ ለባሽ ጥቁር ለባሽ እያሉ አሸባሪ ወራሪ እያሉ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን ፕሮፓጋንዳ በመለፈፍ ይኽው በህዝቡ ላይ ታሪካዊ ጥለት አጥልተው ሊያልፉ ነው፡፡
……. አረጋዊውን ባንቀልባ ከምንሸከም እንኮኮ
ጎልማሳውን ከወኔ ጣር ካልፈታን ኮፍሱት ሞሮኮ
እንደወዶ ገባ ወደል መጠለሉን ከሴት ታኮ
ካቃተን ምንድን ነን እኮ
አየሽ አንቺ እማማ ኢትዮጵያ አየሽ አንቺ እናት አለም
ቃል የእምምነት ዕዳ ነው እንጂ የእናት አባት እኮ አይደለም
ሲል አረጋዊውን ከነጉዱፋ ከምንሸከም ወጣቱንም ወኔ አልባ ሆኖ ዝም ከምንል እንቅስቃሴው ነው ብሒሉ እናም ቃል የእምነቱን የማተባችን ለህሊናችን እዳ እንጂ አራሳችንን በራሳችን እመንታመንበት ቁልፍ እንጂ ከናት ከባት የወረስነው አንዳይደለ ሊሆንም እንደማይችል ነው የሚለው አሁንም እያልን ያለነው ይህኑ ነው፡፡ እናም ባለታሪኩ እሚረዳው ሲያጣ የሀገር ፍቅር ሲሸረሸር ሲያይ ለነዚህ ጉደኞች አሚፋረዳቸዉ ሌላም ቁጪ የላቸው እንዲህ ከናቁኝ እራሴው እቀጣቸዋለሁ ሲል፡-
…… ኢትዮጵያ አምላክሽ አይማረኝ እንደ እጃቸው ባልሰጣቸው
ባንቺ ላይ የጨከኑትን ጭካኔ እኔ ባልከፍላቸው
አንድነትሽን ለመግደል ለዶለቱት ክፋታቸው
እሱ አይማረኝ ብምራቸው
ይላል፡፡
በደል በቀል ጥሩ ባይሆንም ለክፋት ጦርነት መልስ ባይሆንም ነገር ግን እጅግ ከልኬት የዘለለለ የሀገር ፍቅሩ የህዝብ የደሀ ወገን ተቆርቋሪነቱ የተፈጠረበት እትብቱ የተቀበረበት ሀገር፣ ጭቆና የጥቂት ስግብግቦች ገዥዎች መኖር ቢያበሳጨው ነው እንግዲህ ለፈጣሪው አትማረኝ ብሎ መሀላ እስከመፈፀም ያደረሰው፡፡ በአጠቃላይ ከዚያ ዘመን እውነትና ከሎሬቱ ተውኔት እውነት ቀድተን ዛሬ ላይ እዉነታችንን ገሀዳችንን ቃኝተን እኛም የዚህ ዘመን ወኪሎች የራሳችንን አሻራ እንጥል ዘንድ፣ ከወንበር ጥቅም ይልቅ የሀገርና የማተብ ፍቅር ይበልጥብን ዘንድ እንንቃ፡፡


No comments:

Post a Comment