Friday, December 26, 2014

Pleasure

According to John Stuart Mill’s qualitative distinction among pleasures, Intellectual pleasures are inherently higher than sensual pleasures
ልክ እኮ እንዲህ እንደ ማለት ነው it is better to be Socrates dissatisfied than a fool satisfied.
ባጠቃላይ ከስሜት ደስታ ይልቅ የእውቀት ደስታ ይበልጣል ወይንም ሳያውቁ ከሚደሰቱ ይልቅ እያወቁ መከፋት ይሻላል ማለት ነው፡፡
ወይንም ደግሞ በግልፅ አነጋገር እንደ እኔ አይነቱ ደንቆሮ ከሚደሰት ሶቅራጥስ ቢከፋው ይሻላል ነው ምክኒያቱም እኔ ተደሰትኩ አልተደሰትኩ ምንም አልፈይድም ሶቅራጥስ ወይንም እንደ ሶቅራጥስ አይነቱ ግና በመከፋት ውስጥም ሁኖ በስቃይ ውስጥም ሁኖ ባይመቸውም እንኳን አንዳች ጥልቅ እውቀትን ያፈልቃል ለማለት ነው….

ልዴት



እማይጠዲያው ሰው ታውቃላችሁ….ለምን እንዲያልጠዲያውስ ታውቃላችሁ? ለነገሩ ፊት አይቶ መበየን ለምዶብንይእምናየው ክፉ ፊት ሁሉ ውስጡን ዴስተኛ ሊሆን ይችላል….ለሰው መኖር ያው እጣ ክፍላችን ይመስል አብዝሀው ኢጦቢያዊ የራሱን ትቶ በምን ይሉኛል ለሌላው ይኖራልእንዴው ዛዲያ ግርም አይላችሁም…? ለነገሩ ቢላችሁ ባይላችሁ እኔ ምን አገባኝ እንዴው ወጉን ነውይ….
እና እኔ ዛሬ አልጠዲያኝም ፊቴ እንደው እንደ አንዳይ ቅጭም ብሎ ሰው አላናግር አልስቅ አይገርመኝ አይዴንቀኝ በቃ እንዴው ዝም ብዬ ፊቴን አጨናብሬ እንዴ ንፍጣም በግ ጢግ ጢጉን ጥላ ጥላውን ስሄዲ ነው የዋልሁት….ዛዲያ ግርም አይላችሁም?....ለነገሩ ቢላችሁ ባይላችሁ እኔ ምን አገባኝ እንዴው ወጉን ነውይ….
ሰሞኑን ዴሞ የክቡር እምክቡራን እየሱስ ልዴት ነው አሉበኛ በይህ እንኳን ገና አንዲ 12 ቀን ይቀረዋል ነጮቹ ግና ልዴቱን በማክበር ላይ ናቸው….በነሱ እንግዲህ እየሱስ 2015 ያህል አመት አስቆጠረ ማለት ነው መሰለኝ...እንጃ..በኛ ዴሞ ገና 2007 አመት እየሞላው ነውአንዲ ሰው እንዴት ግን ሁለት እድሜ ይኖረዋልያው እንግዲህ እንዴሰው ካወጋነው እንዴሰው ተገልጦም ነበረ ሀሉን ዘንዲያ ነው እንዴ ሰው እንኳን አደረሰህ ልል የወዴድሁ…..እባክህ እስቲ ልዴትህን ምክንያት በማዲረግ ….ወዲህ ሰሙኑን እንዴው እንዴ ወፍ ብርርርር ብላ የጠፋይብንን ሂሊኮፍተር አስመልስልን..ተያ በኋላም በያመቱ ተልደትህ ጋር ዴርበን ኢሊኮፍተር ባንሰራም የኢሊኮፍተር ባዕል አብረን ስናከብር እንውላለን…..እና ልዴትህ የሰላም የዴስታ እና የብልፅግና ይሁንልህ (ወዴት እንደምትበለፅግ ባላቅም!)….
ልጄ ሆይ ወዴት አለህ ማለትህን ትተሀል አልተውህም ግን አየሱስ?....ካልተውህ ችግር አለ ማለት ነውይእንዴው ሀንተ በላይ ባላቅም ቅሉ በዚች በሰጠኸኝ ቅል በምታክል አናቴ ሳሰላው ግዜልህ ……አምላክ ሁነህ ሁሉን አዋቂ ሁሉን አድራጊ ሳለህ እንደማያውቅ ሁነህ መጠየቅህ ግራ ይገባኛል፡፡ ወዲህ ዴሞ ላንተ ጠበቃ ነን የሚሉ የኔ ቢጤ ሰው ሁነው ሳለ ስላንተ ገና ስተነፍስ ዘለው ሊያንቁኝ እሚዴርሱ ብዙ ናቸው….ግና ሳስበው ሳስበውልህ አንተ አምላክ ነህና ጀሌና ጀለስ እንዲሁም እንዴ መንግስት ጠባቂ ታጣቂ እንዴማያስፈልግህ ተረዳሁ….
እረ እዲያ ብቻ አንተ ይመችህ እኔንም ግን ተመቸኝ አሉ…..ይሄው ዛሬ እንኳን በልዴት ቀንህ ፊቴን ሳይጠዲያው ዋለእረ እንዴው በዚች ምዲር ሁሌም ጠድቶኝ አያውቅ እማምላክን….የዛሬው ባሰይእና በልዴት ቀንህ እንዴት ነው እኔ ዲህነት አንቆ ይዞኝ ፖስት ካርዲ ባልክልህ አንተ አሰዲልኝም….እረ ስዴዲልኝ ግዲ የለህም ዛዲያ ከዶላር ጋር ይሁን !!

Wednesday, December 24, 2014

እየተርገበገቡ ይሆን ወይስ ሁሉም ተማክረው አምፀዋል!?


በስንታየሁ (ካሌብ) አለማየሁ



ትናትና ወደ ብሄራዊ አካባቢ ስሄድ….ብሄራዊ ባንክ ፣ ክቡ ባንክ ወይም ወርቃማው ባንክ እየተባለ የሚጠራው ባንክ ፊት ለፊት ስደርስ የሆነ ነገር አይኔን ያዝ አደረገው….ባንኩ ፊት ለፊት የተሰቀሉ ሁለት ባንዲራዎች አሉ….አንዱ የራሱ የባንኩ ሰማያዊ አስተኔ ባንዲራ ነው….አንዱ ግን የኢትዮጲያ ባለኮከቡ (ድንቄም ባለኮከብ!) ባንዲራ ነው፡፡……
እዛ አካባቢ ያለው ነፋስ መቸም አይደለም በገመድ የተንጠለጠለችን ባንዲራ በሰው ገላ ላይ ያለን ልብስ ለማውለቅ ይፈታተናል…..ያች የኢትዮጲያ ባንዲራ ግን ወይ ንቅንቅ እቴ አንገቷን ደፍታ (አንገት አላት ግን?) እንደ ጨርቅ ለወጉ እንኳን በነፋስ ወዲያና ወዲህ ሳትንቀሳቀስ ….ደሞ ጨርቅ አልክ በሉና አሸባሪ በሉኝ አሉ…ባንዲራ የትኛውም ሀገር እስከዛሬ እሚሰራው ከጨርቅ ነው…የድንጋይ ወይንም የብረት ባንዲራ አይቼ አላውቅም….ነገር ግን ጨርቅነቱን ይጥል ዘንድ ከተራ ቁራጭ እራፊነት ይድን ዘንድ ደማችንን ፣ ወኔያችንን ፣ ራዕያችንንና ብልፅግናችንን ጠቅልለንበታል ከዚህ አንፃር ነው እንግዲህ ባንዲራ ከጨርቅነት የሚያመልጠው፡፡
እናም ያች የጦቢያ ባንዲራ ነፋስ ባጠገቧ ሲያልፍ ባላየ ላሽ አላለችላችሁም….ባንዲራ በመርገብገብ ብዛት የሆነ አስፈሪ ሞገድ ይፈጥር ነበረ እኮ!! ወይኔ ነፋስ ባልጠፋበት ሀገር በባንዲራም እስቲ የነ ነበረ ሀገር ልንባል ነው!!.....እረ ምን አለመውለብለብ ብቻ መልኳ እራሱ ጠፍቶ ከወርቃማ ባንክ ፊት ለፊት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ እሚሉት ከለር ምን ይሰራል የተባለ ይመስል…..ከአቧራው ብዛት የተነሳ ይመስለኛል እንደ አይጥማ አይነት ከለርም ተጎናፅፋለች!.......ያች የሀገር ምልክት ፣ ያች ጀግኖች የተዋደቁላት ገለመሌ ብለን እምንለፍፍላት ጨርቃችን እጅጉን ተበሳቁላለች…….
በቃ ሳያት አንጀቴ ልውስ አለ..ሆዴ ተሸበረ….አንድ እማውቃት ምስኪን ሴት ተበድላ መንገድ ዳር አፈር ጎርሳ አፈር ልሳ ያየኋት ያህልም አዘንኩ…..እንባም ተናነቀኝ መንገድ ላይ ተገትሬ ቀረሁ…
ምን ተበድላ ይሆን ስል አሰብኩ…..ባንዲራ ይበደላል እንዴ ይለኛል ሌላኛው እኔ…..ቀላል ይበደላል….ከራሴው ጋር ጭቅጭቅ…ንትርክ ገጠምኩ…
ባንዲራ ለካ ያኮርፋል…..ካከረፈ ደሞ አውሎ ነፋስም ምንም አያርገበግበውም….ሰው ትንሽ በነፋስ አይነቃነቅም ይቅርታ ሰው አልኩ እንዴ….ለነገሩ ባንዲራ ሰው ማለት እኮ ነው ያውም ግብዳ ሰው…. ሶስት አይነት ቀለም የተቀባ ሀገርን የወከለ በነፋስ ተርገብጋቢ ሰው …..
ይሄ አካል ነው እንግዲህ የተሰቀለበት ብረት ላይ ስእል መስሎ ፣ ክንፉን የተመታ አሞራ የተገነጠለ ክንፉን ትቶት ሄዶ…ተንጠልጥሎ የቀረ ግዑዝ አካል መስሎ ያየሁት…..
ግን ባንዲራ ለምን አኮረፈ አንልም?…..ይመስለኛል ወክለኸናል ያልነው ህዝብ ስንዋሽ ፣ ስናጭበረብር ፣ ሀገር ስንክድ (ያው የሰሞኑን ኢሊኮፍተር ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል ) ፣ ሙስና ስናረግዝ ስንወልድ ኮትኩተን ስናሳድግ ፣ ጀግንነት ከደጃችን አይደለም ከውስጣችን ሲመክን ፣ አንዴ የኢሊሙናቴ አንዴ የአንበሳ ምናምን እየሳልን የስእል ደብተር ስናረገው……በነዚህና በሌሎች ባልተጠቀሱ እልፍ አእላፍ ምክኒያቶች ባንዲራው ያኮረፈ ይመስለኛል፡፡

እኔ እግር ጥሎኝ አንዱን ባንዲራ አየሁ…እስቲ በየትምህርት ቤታችሁ በየመስሪያ ቤታችሁ በየሆቴሉ የተሰቀሉትን ልብ እንበል ጎበዝ እየተርገበገቡ ይሆን ወይስ ሁሉም ተማክረው አምፀዋል!?.......ለነገሩ የቤተ መንግስቷ ከተርገበገበች ሀገር ለመወከል ትበቃለች መሰለኝ!!