Tuesday, November 11, 2014

ኢትዮጵኛ

ምን እንደናፈቀኝ ታውቃላችሁ ኢትዮጲያዊነት…..
አዎ እድግመዋለሁ ኢትዮጲያዊነት……አቤት አዳሜ ይሄኔ ገና እንዲህ እሚል ቃል ሲሰማ…..ኤኤኤጭ ደሞ ጀመረው እንግዲህ ፖለቲካ ሊያወራ እሚል ይኖራል….እኔ ግን በፍፁም ፖለቲካ አይደለም እማወራው…..ኢትዮጵኛ ነገር እንኑር ነው…..

ኢትዮጵኛ ማለት ምን ማለት ነው……እንደ አለማቀፍ እያሰብን እንደ ኢትዮጵያ መኖር (በእርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ተሁኖ እንደ አሜሪካ ልኑርስ ቢባል እንዴት ይቻላል!) ፣ ከምንም በላይና ከምንም በፊት ስለ ኢትዮጵያ ማወቅና ለማወቅ መፈለግ ያስፈልጋል….ዛሬ ስለ ኢትዮጵያ ከማወቅና ከማንበብ ይልቅ ስለ ኦባማ ስልጣን መልቀቅ አለመልቀቅ እሚጨንቀን ወይንም በቃ ስለነሱ ማውራት ስልጣኔ መስሎ እሚታየን ጥቂት አይደለንም ……ስለነባራዊ ሀቅና ኑሯችን ከማውጋት ይልቅ ስለስፖርት ማውራት ደስ ይለናል……አለም አቀፍ እውቀትን እንደው የእውነት በትክክለኛው ጊዜ መረጃ ከጨበጥን እሰየው ነው…….ነገር ግን ቅድሚያ ስለደጃችን ብናውቅ፣ ስለ ራሳችን ብንመረምር ደስ ስለሚለኝ ነው ደስ ስለሚለኝ ብቻም ሳይሆን ትክክለኛውም መንገድ ስለሆነ ነው……..
ሌላው ደግሞ ባህላችንን ሳናፍርበት መኖር ለምሳሌ ባህል ስንል አለባበስን አነጋገርን አመትባል አከባበርን ፣ አጨፋፈርን አበላልንና አጠጣጥን ሁሉ ይጨምራል ፣ ……ቋንቋችንንም ከሌላው ሀገር ቋንቋ ጋር ሳንበርዝ ጥርት አርገን ማወቅና ማውጋት ….በተለይ ስለ ቋንቋ ሲነሳ ብዙ ጊዜ እንደተባለው……እንግሊዝኛ ማውራት በቃ የስልጣኔ ምልክት ከመሆኑም በዘለለ አዋቂ ነው ብለን የሆነ ሰውን ለመጠርጠር እንግሊዝኛ መናገር መቻል አለበት…..እንግሊኛን ማወቅ አሁንም ነውሩ አይታየኝም ነገር ግን ….ነውር የሆነው፡-
አማርኛ ተናጋሪ ወይንም ሀበሻ ኢትዮጲያዊን ሰብስበን በየመሀሉ እንግሊዝኛ ጣልቃ ያስገባን ስንናገር ነው ፣ እንግሊዝኛን ማወቅ ብቻ የእውቀት  መለኪያ አድርገን ስንቀበል ነው ፣ መላ ሀገር በሚከታተለው የቴሌቪዥን መስኮት የሚለቀቅን ሙዚቃ በእንግሊዝኛ በርዞ ሲቀርብ….ኢትዮጵኛ ባልሆነ አነጋገርና ልሳን ሲቀርብ ነው ፣ የራሳችን ብሄራዊ ቋንቋ እያለን በስልኮቻችን መልዕክት በእንግሊዝኛ ስንለዋወጥ ነው ፣ የተለያየሁ ብሄራዊ ጉዳዮችን ለምሳሌ….ከ EBC እራሱ ብንነሳ ኢ ቢ ሲ ምንኛ ነው….. EBC እሚለውን ትርጉም በአማርኛ መተርጎም አልተቻለም ወይ? ፣
የኢትዮጲያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ማለትስ ምንድን ነው ? ፣ ሌሎችም እጅግ በጣም ለቁጥር የሚያታክቱ ማስታወቂያዎችን ፣ የሆቴል ስሞችን ፣ የንግድ ስሞችን ፣ የትምህርት ቤት የመስጊድ የቤተ ክርስቲያን ስሞችን ፣ የሆስፒታል ስሞችን ፣ የማሰልጠኛና የምርምር ቦታዎች ስሞችን በእንግሊዝኛ ስንጠቀም ነው እንግሊዝኛ ነውር የሚሆነው ፣……..ምክኒያቱም እኛ ኢትዮጲያዊ እንጂ እንግሊዛዊ አይደለንማ…እንዴት ነው ነገሩ….፣ .ምንም አስከዳጅና አስቸጋሪ ሁኔታ በሌለበት ቀድሞ እንግሊዝኛ ስም መለጠፍ ፣ ኢትዮጲያዊን ለሚያስተናግዱበት መስሪያ ቤት ወይንም ት/ቤት ወይንም ሆስፒታል ወይንም ሆቴል በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማውጋት ምን ይሉታል……..?
ሌላው እና ወሳኙ ደግሞ …ንባብና ውይይት ነው….ይሄን ሁሉ የማንነታችንን እጦት ሊገነባልን የሚችለው ንባብ ነው…..እራሳችንን በእውቀት ለማነፅ ሰው በመሆናችን ብቻ ማንበብ ግድ ነው አለቀ…..ከዛ ያነበብነውን ነገር መወያየትና ማጋራት…......ቆይ ዝምታ የኛ ሀገር ባህል ነው ያለው ማነው እረ? ……
ሁለት አይነት ተረት አለን እኮ ስለ ንግግር…እንደየ አስፈላጊነቱ እንድንቀሳቀስ ለምሳሌ፡ ….‹‹ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባበትም›› እና ‹‹ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል›› ………..
አሁን ዝንብ እንዳይገባብን እየከለከልን ደጃዝማችነቱ ሳይሆን እሱስ ሲያምረን ይቅር…መቸም!!….ካነበብነውና በምንኖረው ጉዳይ ላይ መወያየቱ ማውራቱ ሀሳብ መካፈሉ እንዳይቀር መነጋገር ግድ ነው ….ደግሞም እኮ ከፖለቲካ ውጭ መነጋገር የተፈቀደ ይመስለኛል አኛ ሀገር …..እ……አይደለም እንዴ ? ቅቅቅ!…….
አሁን አሁን በተለይ አዲስ አበባ ላለነው…..እድሜ ለሰልፍ…እንጂ …....ለታክሲ ፣ ለዳቦ ፣ ለነዳጅ ፣ ለዘይት ፣ ለስኳር ፣ ስራ ለመወዳደር ብዙ ብዙ ሌሎችም ያልጠቀሱ ሰልፎች ከብዙ ሰአት በላይ እንቆማለን……ክፍለ ሀገርም ብንሄድ….ብዙ አይነት የመገናኛ እና የመሰባሰቢያ መንገዶችና አጋጣሚዎች አሉ ….ታዲያ …..በዚህ ሁሉ ሰልፍ እና መሰባሰብ ላይ ህዝቡን ስታዩት የተኳረፈ ይመስላል….የማይተዋወቅ የተለያየ ሀገር ዜጋ ይመስላል …..አንድ የሆነ አንድ እሚያደርገን ብዙ እሚያወያዩን ጉዳዮች እያሉ……ገና እንዲህ ባወራስ ፖለቲካ ነው ብሎ ሰው ወደ ሌላ አተያይ ቢቀይረውስ…. አይነት…..ፍራቻ አጥሮን አንድ ላይ ሁነን ተለያይተናል……..በጣም ተራርቀናል እረ………
ያለፈው ትውልድ በተለይ የተማረ እሚባለው ትውልድ ያነብ ነበረ…..ይነጋገር ይወያይ ነበረ…….በራሱ ቋንቋና አልባሳት ይቅርና በክላሹና በመድፉ ይኮራ ይጀነን ነበረ………ኢትዮጲያዊነት ደስ ይለው ነበረ………ስለዚህ ነበረ ነበረ ነበረ…..እያልን ነበረን እየደገምን ከምንኖር……እኛው በኛው እራሳችንን መውደድና መተሳሰር ማንነታችንን ከፈረንጅ አስበልጠን መውደድ ….እሩቃችን አይመስለኝም…….
በአጠቃላይ እጦታችን ፍቅርና አንድነት ነው ፣ ማንነትን አለማክበርና እራሳችንን ጭምር ንቀን ነጭን ማምለክ ነው ፣ በራስ ነገር ያለመኩራትና ስለ ራስ ለማወቅም አለመፈለግ ነው ….ምንም ሳንሞክረው ስለ ራሳችን ጉዳይ ያተኮረ እውቀትን መሰልቸትና መናቅ ነው……….ሲመስለኝ ታዲያ የዚህ በሽታችን ሀኪምና ሆስፒታል እኛው ራሳችን ነን፡፡


No comments:

Post a Comment